የደቡብ ክልል ለክልል ማዕከላት ከ8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

0
549

ደቡብ ክልል መስከረም 22፣ 2012 ባካሄደው 203ኛ መደበኛ ስብሰባ የክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶችን የ2012 የመደበኛና ካፒታል በጀት ላይ ምክክር በማድርግ በበጀት ዓመቱ ለክልል ማዕከል ከ8 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጽድቋል።

ከዚህ ውስጥ ለመደበኛና ለካፒታል ወጪ 4 ቢሊየን ብር፣ ለክልላዊ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ 3 ነጥብ አንድ ቢሊየን እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር እና ለመጠባበቂያ 200 ሚሊየን ብር መመደቡን የርዕሰ መስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።

ቀደም ሲል በክልሉ ተዘጋጅተው ተግባራዊ የተደረጉ የበጀት አስተዳደር መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ ነው ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመደበኛ በጀት አመዳደብን ታሳቢ ያደረገው ተብሏል።

የዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በፌዴራል መንግስት የገንዘብ ሚኒስቴር በተዘጋጀው መመሪያ መሰረት ለክልሎች የሚመደበው ውስን አላማ ያለው የፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የድጎማ በጀት ማዋል የሚችለው በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይም ለአግሮ እንዱስትሪ ማስፋፊ ፕሮጀክቶች መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህ መሰረትም ለይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ለሚገኙ 31 የክላስተር ማዕከላት ግንባታ ማጠናቀቂያ ድጋፍ እንዲሆን መወሰኑን የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

‹‹መስተዳድር ም/ቤቱ የክልላዊ ፕሮግራም ፕሮጀክቶች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ፣ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ተዘዋዋሪ ፈንድ፣ ባለፉት በጀት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመስኖ ግንባታና የቴክኒክና ሙያ ግንባታ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል በጀት በመደልደል በበጀት እንዲደገፉ ውሳኔ አስተላልፏል።››

ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here