መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየኢትዮጵያ አየርመንገድ በምዕራብ አፍሪካ የአቪዬሽን አካዳሚ ሊያቋቁም ነው

የኢትዮጵያ አየርመንገድ በምዕራብ አፍሪካ የአቪዬሽን አካዳሚ ሊያቋቁም ነው

ዕረቡ ሰኔ 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየርመንገድ በምዕራብ አፍሪካ የአቪዬሽን ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱ ተገለፀ።

የአየርመንገዱ አቪዬሽን አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር መሳይ ሽፈራሁ ከኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፤ በቶጎ ሎሜ ከሚገኘው አስካይ አየርመንገድ ጋር በሽርክና የአቪዬሽን አካዳሚ ለማቋቋም ድርድር እየተካሄደ ነው።

ድርድሩ ከተሳካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአስካይ አየርመንገድ ጋር በጋራ የአውሮፕላን አብራሪዎች ፤ ቴክኒሺያኖች እና የበረራ አስተናጋጆች ማሰልጠኛ ተቋም በቶጎ ዋና ከተማ ሎሜ እንደሚያቋቁሙ መሳይ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ከአስካይ መስራች ባለአክሲዮኖች መካከል አንዱ ሲሆን፤ አየርመንገዱን የማስተዳደር እና የቴክኒክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች