የአስጌ ዴንዳሾ የጥበብ ጉዞ በጨረፍታ

0
960

“ዴንዳሾ“ በሚለው ነጠላ ዜማው እና በአስደማሚ ሳቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ በቀላሉ መግባት የቻለው አስጌኘው አሻኮ ውልደቱ በደቡባዊቷ የአትዮጵያ ክፍል ጋሞ ጎፋ ሲሆን አስጌኘው አሻኮ ባጋጣሚ ነበር በወላይታ በነበረ ፕሮግራም ላይ ግጥም ሲያቀርብ ዘፋኝ የመሆን እድሉን ያገኘው፡፡ይህንን ችሎታውን በመረዳት የተለያዩ ነጠላ ዘፈኖቹን ለአድማጭ ጆሮ በማድረስ በሃገር ወሰጥና ከሃገር ወጭ የሚኖሩ የብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ መግባት የቻለው፡፡ ከ 15 በሚብልጡ ሃገሮችና በ 3 አህጉራት የሙዚቃ ስራውን በማቅረብ የተለያዩ አድናቄዎችን ማፍራት የቻለው ሙዚቀኛ በዩቲዩብ ላይም በስምንቱ ነጠላ ዜማዎቹ አማካኝነት ከ12 ሚሊዮን ተመልካቾች በላይ አግኝቷል።

ከስድስት አመት በፊት ከ አዲስ አበባ በ 313 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ወላይታ መደበኛ ኑሮውን ይመራ የነበርው አስጌ መድሃኒት በሚያከፋፍል ድርጅት ውስጥ ሂሳብ ሰራተኛ ሆኖ በመስራት በወር 700 ብር ይከፈለው ነበር፡፡በነዚህ ግዜያት ውስጥ አንድ ቀን የመዝፈን ክህሎት አለኝ ብሎ አያውቅም። ነገር ግን በ 2006 ዓ.ም በ አንድ አጋጣሚ በተለያዩ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በተዘጋጀው ስለ ኤች አይ ቪ እና ስለ ቤተሰብ ምጣኔ በሚያስተምረው ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የቻለው ሙዢቀኛ ከዛም በኃላ ነበር ህይወቱን መቀየር የቻለው፡፡

በፕሮግራሙ ላይም ስራውን በማቅረብ ላይ እያለ ነበር የሙዚቃ ደረሲው ሸዋአገኘው ሳሙኤልን ቀልብ መሳብ የቻለው። ሸዋአገኘውም ፤የሙዚቃ ችሎታ እንዳለኝ በሚነግረኝ ግዜ ግራ ገብቶኝ ነበር ይላል አስጌ ፤ምክንያቱም ከዚህ በፊት የሙዚቃ አለም ውስጥ እገባለው የሚል አሳብ በውስጤ ካለመኖሩም ባሻገር ማንም ሰው የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንድገባ አበረታቶኝም ሆነ ጭሎታ እንዳለኝ ነግሮኝ ስለማያውቅ እውነታውን አምኖ መቀበል አቅቶኝ ነበር። ሆኖም ግን ከሸዋአገኘው የተሰጠኝን አስተያየት በመቀበል ነበር ወደ ሙዚቃ ሕይወት ውስጥ መግባት የቻልኩት ይላል፡፡

በሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ የራሱን የሆነ ቦታ ማግኘት የቻለው እና ከ አምስት አመት በፊት በሳቂታነቱ ይታወቅ የነበረው አስጌ በአሁኑ ሰዓት ከደቡባዊቷ ኢትዮጵያ ከመጡ ታዋቂ ዘፋኞች መካከል አንዱ ነው፡፡እስካሁን በህዝቡ ጥሩ ተቀባይነት ያስገኙለትን 8 ነጠላ ዜማዎችን ለአድማጭ ያቀረበ ሲሆን በነዚህም ነጠላ ዜማዎቹ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን አፍርቷል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ባላቸው Coke Africa ላይም ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው አስጌ “ዱብድ ያዲሴ“ የሚለው ሙዚቃው በዩቲዩብ ላይ ከ4 ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን በማግኘት በሀገሪቱ ታዋቂ ሙዚቃ ሆኗል፡፡

ውልደቱም በ ጋሞ ጎፋ ዞን ጪማ ጫሞ ከተማ ሲሆን ለቤተሰቡም አራተኛ ልጅ ነው። በልጅነቱም ካጋጠሙት መጥፎ አጋጣሚዎች መካከል የአምስተኛ ክፍል ተማሪ በነበረበት ወቅት ወላጅ አባቱን በሞት ያጣበት አጋጣሚ ለሱ በጣም አሳዛኝና አስቸጋሪ የህይወቱ አጋጣሚ እንደነበር አስታውሷል፡፡በወቅቱ የቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበሩት እና በሹፍርና ስራ ላይ የተሰማሩት አባቱ በሞት ከተለዩአቸው በኃላ ወላጅ እናቱ ልጆቻቸውን ለመመገብ ቀን ተሌት ደፋ ቀና ሲሉ ቆይተው ይህን መቋቋም ሲከብዳቸው ነበር ከዘመዶቻቸው እርዳታን ለማግኘት ወደ ወላይታ ሶዶ ለመሰደድ የተገደዱት፡፡

አስጌም በዚህን ወቅት ነበር ትምህርትን እንደ ዋና ቁልፍ በመጠቀም ድህነትን መታገል የጀመረው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱ ላይም ከፍተኛ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ተማሪዎች መካከል የሚጠቀስ ሲሆን ከትምህርቱም ጎን ለጎንም ቤተሰቡን በሊስትሮ ሙያነት እና ስኳር ድንች በመሸጥ ቤተሰቡን ይደግፍ ነበር፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱንም ካጠናቀቀ በኃላ ነገሮች እየተባባሱ መጡ የሚለው ሙዚቀኛ ፤ለቤተሰቦቼ ተጨማሪ ሸክም ላለመሆን ከቤተሰቤ ቤት በመውጣት ጎዳና ላይ ለመኖር ተገደድኩ ይላል፡፡ አስጌ በነዚህ ፈተናዎች ውስጥ ተስፋ አልቆረጠም ነበር ። ለትምህርቱም የበለጠ ትኩረት መስጠቱን ቀጠለ ይህ ውሳኔውም ከወላይታ ቴክኒክና ሙያ ማእከል በአካውንቲንግ ዲግሪውን እንዲያገኝ እረድቶታል፡፡

ሙሉ ለሙሉ ሙዚቃ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከመግባቱ በፊት በአለም አቀፍ የታወቁ ሙዚቀኞች ውስጥ Akon, P-Square እና May-D ሙዚቃዎችን እንደገና የሃገሩን ሰው በሚመጥን መልኩ ይሰራ ነበር፡፡ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሙዚቃው ኢንዱስትሪ ከገባ በኃላ ኦሪጅናል የሆኑ ሙዚቃዎችን መስራት ጀመረ፡፡በአጭር ጊዜ ውስጥም የመጀመሪያ ነጠላ ዘፈኑን “ዴንዳ“የተሰኘውን ዘፈን ለህዝቡ ጆሮ ማድረስ ቻለ፡፡

የህዝቡ ልብ ውስጥ በቀላሉ መግባት የቻለው ሙዚቀኛም ከተወዳጅነቱም የተነሳ የተለያዩ አይነት ማህበረሰቦች እና የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ያንጎራጉሩለት ነበር፡፡ የብዙሃኑንም ልብ ካሸነፈ በኃላም 15 በሚሆኑ የተለያዩ ሃገሮች በመሄድ ሙዚቃውን ማቅረብ ችሏል በዚህም በአንድ መድረክ ከ 3000 – 5000 የ አሜሪካ ዶላር ያገኛል፡፡ በ 2017 እ.ኤ.አ በአምስተኛው ዙር Coke Studio ላይ በመገኘት ከ አቻው ኡጋንዳዊታ ታዋቂ ዘፋኝና ዳንሰኛ ጋር በመጣመር ዘፍኗል።

አስጌም ትልቅ የሆነውን የሃገሩን ባህል ለተቀረው አለም የማሳየት ትልቅ ፍላጎት ስላለው በተለያዩ መድረኮች ላይ ሲቀርብም የተለያዩ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችን ባህል የሚያንፀባርቁ ልብሶችን በመልበስ ሃገሩን ያስተዋውቃል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኘው ሙዚቃ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ከሚዘወተሩ ሙዚቃዎች ጋር ይመሳሰላል የሚለው አስጌ ፤ ልክ እንደሌሎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ሙዚቃ የኢትዮጵያ ሙዚቃ እንዳላደገም ተናግሯል።ለኔ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አለማደጉ ዋናው ምክንያት በ ሙዚቀኞች መካከል አብሮ የመስራትና የመተባበር ባህል ማነሱ ብሏል። እሱ እንዳለውም “አዛኛውን ታዋቂ ሙዚቀኞች የነሱን ልምድ ለሌላ ሙዚቀኛ አያካፍሉም ወይም ደግሞ ጀማሪ አርቲስቶችን አያበረታቱም አንዳንዴም ጥሩ አቅምና ችሎታ ያላቸውን አርቲስቶችን ያጣጥላሉ “ብሎ ገልጾታል።

አሁን ባለው ትውልድ ላይም ቅሬታ ተሰምቶኛል ምክንያቱም ደግሞ ያሁኑ ትውልድ ለምእራብያኑ ስልጣኔ ነው ቅድምያ የሚሰጠው የራሳቸውን የሆነውን ነገር ጥለው የሌላውን ባህልና ስልጣኔ ለማንሳት ይታገላሉ ይህ ደግሞ የሙዚቃውን ኢንዱስትሪ እንዳያድግ የራሱን አስተዋጾ ያደርጋል ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከምራብያኑ ሙዚቃ ይልቅ ለሀገራቸውን ሙዚቃ መቀበል እንዳለባቸውም ተናግሯል።

አስጌ እንዳለው በአሁኑ ሰአት ለሙዚቃው ኢንዱስትሪ አለማደግ ትልቅ ማነቆ የሆነው ሙዚቃው ላይ ኢንቨስት የሚያደርጉ ኢንቪስተሮች ፍላጎት ማነስ ነው ፡፡ነገር ግን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ካልተናቀ እና ቸል ካልተባለ ሙዚቀኛውንም ሆነ ኢንቪስተሩን የሚያሳድግ ይሆናል ሲል ተናግሯል።
“ለሙዚቃው ኢንዱስትሪ ማደግ ሌላኛው ማነቆ የሆነው ችግር የ copyright ስምምነት መብት መጣስ ነው“ የሚለው ሙዚቀኛም እንደሱ ላሉ ታዋቂ ሙዚቀኞችም ይህ ችግር በጣም አሳሳቢ ነው።

በእጁ ላይ 40 የተጠናቀቁ ሙዚቃዎች ቢኖሩትም ይህን ችግር በመፍራት አልበሙን የሚለቅበት ቀን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራዘመ ነው ፤ሆኖም ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ አልበሜን ላዘግየው እንጂ ይህንን ችግር ተጋፍጪ አልበሜን መልቀቄ እማይቀር ነው ብሏል።

አያይዞም የተለያዩ ሙዚቃዎቹን እንዲሁም ወደፊት የሚለቃቸውን በተለያየ ቋንቋዎች ያዜማቸውን ሙዚቃዎች በአማረኛ፣ ትግረኛ፣ኦሮመኛ፣ሲዳመኛ እና ጋሞኛን ቋንቋዎችን የያዙ ሲሆን ይህን አልበሙን በራሱ ለማስተዋወቅ የዩቱዩብ ቻናል ከፍቷል፡፡በተጨማሪም የተለያዩ ጡረታ የወጡ አርቲስቶች ላይ የደረሰውን የኢኮኖሚ ችግር በማየት ከነሱ በመማር ኢንቪስተመንቶች ላይ በመሳተፍ ወደፊት የራሱን ቢዝነስ እንደሚጀምርም ተናግሯል፡፡
ከፕሮፊሽናል ህይወቱም ስንወጣ አስጌ እጮኛውን በቅርቡ ለማግባት እንዳቀደ አጫውቶናል፡፡
ከኢትዮጵያ ቢዝነስ ሪቪው ለአዲስ ማለዳ እንዲመች ተደርጎ በመሰረት አበጀ የተተረጎመ

ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here