የአፍሪካ ቀንድ ንግድን የሚያቀላጥፍ ፍኖተ ካርታ ጸደቀ

0
993

የምሥራቅ አፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማቀላጠፍ ያግዛል የተባለ ፍኖተ ካርታ ማጽደቃቸው ተሰምቷል።

የምሥራቅ አፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮች የንግድ ፍኖተ ካርታውን አተገባበር ሁኔታን ለመገምገም እና ቀጠናዊ ውህደትን ለማጠናከር መወሰድ ስላለባቸው ፖሊሲዎች በበይነ መረብ ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ በፋይናንስ ፕሮጀክቶች አቅርቦት መሻሻል መታየቱን የገለጹ ሲሆን፣ በቅርቡም ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚሆን የ325 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከዓለም ባንክ ጋር መፈራረማቸውን ገልጸዋል።

የአገራቱ የገንዘብ ሚኒስትሮችም የምሥራቅ አፍሪካ የንግድ ትስስር ማጠናከሪያ ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል። በፋይናንስ ሚኒስቴር የንግድና ቀጠናዊ ውህደት ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ በበኩላቸው፣ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ዘዴን በመጠቀም ፍኖተ ካርታውን ተግባራዊ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ፣ የኬንያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የደቡብ ሱዳን የገንዘብና ንግድ ሚኒስትሮች እንዲሁም የዓለም ባንክ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ኢጋድን ጨምሮ ሌሎች አጋር አካላት ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በፈረንጆቹ 2019 የተመሠረተ ሲሆን፣ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተጀመረውን ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ዓለም ባንክ እና በአውሮፓ ኅብረት በሚገኝ ድጋፍ በትብብር ለመሥራት የተቋቋመ ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 191 ሰኔ 25 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here