መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 ያለእድሜ ጋብቻ በከፍተኛ መጠን የታየባቸው አገራት

10 ያለእድሜ ጋብቻ በከፍተኛ መጠን የታየባቸው አገራት

ምንጭ፡-ስታቲስታ (2022)

ያለእድሜ ጋብቻ የቆየ እንጂ አሁን ዘመናዊ ነኝ በምትል ዓለም የሚተገበር አይመስልም። ነገር ግን ይህ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሆነ፣ ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት ልጆችን ለጋብቻ መስጠት አሁንም በተግባር ሲፈጸም ይታያል። ሕግና ደንብ ቢወጣና ቢሻሻልም፣ በጉዳዩ ላይ ፍጹም የሆነን መፍትሄ ማምጣት ግን የተቻለ አይመስልም፡፡

ይህን በሚመለከትም ስታቲስታ የተባለው ድረ ገጽ ከኹለት ዓመት በፊት ጀምሮ ምን ያህል ልጆች ያለእድሜያቸው ተዳሩ የሚለውን በአሀዝ ዘርዝሮ አስቀምጧል። በዚህ መሠረት ሕንድ ከዓለማችን በርካታ ሕጻናት ልጆችን ለጋብቻ የሚሰጡባት አገር በመሆን ቀዳሚ ናት። በአውሮፓውያን የዘመን ቀመር ከ2020 ጀምሮ በሕንድ 15.6 ሚሊዮን በላይ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ተድረዋል። ባንግላዲሽ በ4.4 ሚሊዮን እንዲሁም ናይጄሪያ በ3.7 ሚሊዮን ሲከተሉ፣ ኢትዮጵያ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።


ቅጽ 4 ቁጥር 191 ሰኔ 25 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች