የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ላይ ድርሻ ሊገዛ ነው

0
1070

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ድርሻ ለመግዛት ሃሳብ ማቅረቡ ታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ተወልደ ገብረማሪያም እንዳስታወቁት የደቡብ አፍሪካን አየር መንገድ ለመርዳት እና የደቡብ አፍሪካ መንግሰት ፈቃደኝቱን ካሳየ ኢትዮጵያ አየር መንግድ ከደቡብ አፍሪካው አቻ  አየር መንገዱ ላይ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው መጠቆማቸውን ዲጂታል ስታንዳርድ ዘግቧል።

የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ከፈረንጆች 2011 ጀምሮ ምንም ትርፍ ያላስመዘገበ እና ከሳምንት በፊት ማሳወቅ የነበረበትን ገቢ በተፈጠረበት የገንዘብ ችግር ሳያሳውቅ ቀርቷል። አየር መንገዱ አሁን ባለበት ደረጃ 9 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉ እና ግንባር ቀደም ትርፋማ አየር መንገድ አንዱ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ የደቡብ አፍሪካው እና የኤንያ አየር መንገድ በኪሳራ ውስጥ እንደሚገኙ የተለያዩ የአቪየሽን ዜና አውታሮች እየዘገቡት ይገኛሉ።

የደቡብ አፍሪካ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር አላያንስ አባላት መሆናቸው የሚታወቅ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here