- የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ዛሬ መስከረም 26/2012 የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በይፋ የከፈቱ ሲሆን በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የዲፕሮሎማት ማኅበረሰብ፣ የሐይማት መሪዎች ተገኝተዋል። (አዲስ ማለዳ)
………………………………………………………………………
- ባለፉት 17 ቀናት በገቢ ኮንትሮባንድነት ከ1ነጥብ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጦር መሳሪያን ጨምሮ ሌሎች 55,664,791 ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን ታዉቋል።በወጪ ኮንትሮባንድም 7 ነጥብ7 ብር የሚገመት የዉጪ ምንዛሬ፤2ነጥብ 5 ብር የሚያወጡ የቁም እንስሳት፤1ነጥብ,8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ነዳጅና ሌሎች 3ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ እቃዎች በድምሩ 15,728,318 ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ከአገር ሊወጡ ሲሉ መያዛቸዉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታዉቋል። (አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………….
- በተያዘው በጀት ዓመት 150 የሚሆኑ በግልና በመንግሥት አጋርነት የሚገነቡ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኹለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ወቅት ተናገሩ። (አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………………….
…………………………………………………….
- በኢትዮጵያ ተቀማጭ የሆኑ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ያለውን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ እንዲሳተፉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጥሪ አቅርበዋል።አምባሳደሮቹ በክልሉ ለኹለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል። (ዋልታ)
…………………………………………………..
- በኢጋድ አባል አገራት በአጠቃላይ ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የውስጥ መፈናቀል መከሰቱን በ12ተኛው የኢጋድ አባል አገራትጉባዔ ላይ ተገልጿል።የኢጋድ አባል አገራት የፈረሙትና ኢትዮጵያ የሌለችበት የካምፓላ ስምምነት በደቡብ ሱዳን ተግባራዊ ተደርጎ ለውጥ በማምጣት ላይ መሆኑ ታዉቋል።ጉባዔው ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የሚፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው በመመለስ ለዘለቄታው ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።(ኢቢሲ)
…………………………………………………….
- በጤናው ዘርፍ የመንግስትና የግል ትብብር ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ዛሬ መስከረም 26/2012 በአዲስ አበባ በተጀመረው 4ኛው የአፍሪካ ጤና ቢዝነስ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።ከዓለም አቀፍ ድጋፍ በመንግስት በሚገኙ መድኃኒቶች በመንግስት ተቋማት ብቻ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች ደንበኞቹ ለአገልግሎት ብቻ ከፍለው በግል ጤና ተቋማት እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ከሃምሳ በላይ አገራት የተውጣጡ 300 በላይ ተሳታፊዎች እና 81 ያህል በጤና ላይ የሚሰሩ አጋር አካላት እየተሳተፉ መሆኑ ታዉቋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
………………………………………………
- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ መስከረም 24/2012 በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ5 ሰላማዊ ዜጎች እና 3 የፀጥታ ኃይሎች መሞታቸው ታዉቋል።በአካባቢዉ ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ ከ3 ቀን በፊት አንድ የታጠቀ ግለሰብ የክልሉ ልዩ ኃይል በሚገኝበት የጥበቃ ማማ ላይ በከፈተዉ ተኩስ ነዉ።ግለሰቡ ጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በማይቻልበትና በኮማንድ ፖስት ስር ባለ አካባቢ 3 የእጅ ቦንቦች፤ ክላሽንኮቭ እና በርካታ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱን የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸዉ በቀለ ተናግሯል። (ዶይቸ ቬለ)
……………………………………………………………………………………………..
- በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ቅዳሜ እኩለ ሌሊት በተካሄደው የማራቶን ውድድር ሌሊሳ ዴሲሳ አንደኛ፤ ሞስነት ገረመው ደግሞ ሁለተኛ ሆነው ለኢትዮጵያ ወርቅና ብር አስገኝተዋል።ሌሊሳ 2፡10፡40 በሆነ ሰዓት ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን የራሱን የዓመቱን ምርጥ ውጤት አስመዝግቧል።ሌሊሳ 2፡10፡40 በሆነ ሰዓት ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን የራሱን የዓመቱን ምርጥ ውጤት አስመዝግቧል። (ቢቢሲ)



