“የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት 34 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል”፦የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት

0
1611

ማክሰኞ ሐምሌ 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ መሰረት የሰኔ ወር 2014 አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 34 ከመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለአዲስ ማለዳ የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ፤ የሰኔ ወር 2014 የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ38 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፤ በያዝነው ወር በእህሎችና አትክልት ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ታይቷል፡፡

የሚቀዳ የምግብ ዘይት፣ ዘይትና ቅቤ፣ ቡናና ለስለሳ መጠጦችም ጭማሪ ያሳዩ ቢሆንም ከውጭ የሚመጣው የምግብ ዘይት ላይ መጠነኛ ቅናሽ ተመዝግቧል።

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2014 ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ28 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ፤ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ አነቃቂዎች (ጫት)፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት መስሪያ እቃዎች (የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶ፣ የቤት ኪዳን ቆርቆሮ)፣ የቤት ዕቃዎችና የቤት ማሰገጫዎች፣ ነዳጅ፣ ህክምናና እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የሰኔ ወር 2014 አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ግንቦት ወር 2014 ጋር ሲነፃፀር በ4 ነጥብ 5 ከመቶ እና፤ የምግብ የኢንዴክሱ ክፍሎች በ3 ነጥብ 9 ከመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት በ5 ነጥብ 5 ከመቶ አሳይቷል፡፡

ወርሃዊ የዋጋ ግሽበት ምጣኔው በመጨረሻዎቹ ኹለት ተከታታይ ወራት መካከል ያለውን የዋጋ ለውጥ ለመለካትየሚያገለግል ሲሆን፤ ወርሃዊ የዋጋ ግሽበት ምጣኔው የወቅቱን ኹኔታ የሚያሳይ በመሆኑ የአጭር ጊዜ ክስተቱን ብቻ ያመለክታል ተብሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here