በባህር ዳር ከተማ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሒዷል

0
640

በባህር ዳር ከተማ ዛሬ መስከረም 27/2012 ረፋድ 4 ሰዓት ከ30 ሲል ሰላማዊ ሰልፍ መካሔዱን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ከስፍራው ተናግረዋል። ምንጮች እንደተናገሩት፤ ሰልፉ የተጀመረው ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፍርድ ቤት ውሎ ካበቃ በኋላ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ፍርድ ቤቱም ፖሊስ አቅርቦት ነበረውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ውድቅ ያደረገ ሲሆን እስከ መጪው ጥቅምት 12 ድረስ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በርካታ ቁጥር ያለው ሰው የተሳተፈበት ሕዝባዊ ሰልፍ ፍፁም ሰላማዊ የነበረ ሲሆን ‹‹የግድያው እውነት ይውጣ›› እና ‹‹የታሰሩት መሪዎቻችን ይፈቱ›› የሚሉ መፈክሮች በሰልፈኞቹ ይስተጋቡ እንደነበር አዲስ ማለዳ ምንጮች አስታውቀዋል። የክልሉ ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ፤ አይን እማኞች እንዳረጋገጡትም ፖሊስ ከልክ ያለፈ ኃይልን ተጠቅሞ ነበር ሲሉ ተናግረዋል። ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ30 ላይ ጀመረው  እና ከ300 እስከ 400 ሰዎች ተሳትፈውበታል የተባለው ሕዝባዊ ሰልፍ እስከ 6 ሰዓት ድረስ ዘልቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here