የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ እየተካሔደ ነው

0
852

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድና በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ አማካኝነት የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና በሚል የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ አለም አቀፍ ኮንፍረንስ እየተካሔደ ነው። በአፍሪካ ኅብረት የቀድሞው አዳራሽ እየተካሔደ የሚገኘው ኮንረፍረንሱ በተያዘው ዓመት የሚካሔደውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ኹሉም ባለድርሻ አካላት ለአገራዊ ኹነቱ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሓሳብ ቀርቦበታል። በኮንፍረንሱ ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር የተገኙ ሲሆን አሜሪካ በአገራዊ ምርጫው ላይ የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብተዋል። ለኹለት ቀናት የሚቆይው ኮንፍረንሱ፤ ከዚህ በፊት ከምርቻ ጋር በተበተያያዘ የታዩ ክፈተቶችን ነቅሶ በማውጣት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሔድ ምክክር የሚደረግበት እንደሆነም የብሔራዊ ምርቻ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ አያይዘውም፤ የፀጥታ አካላት ቦርዱ ተሳካ ምርጫ እንዲያደርግ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

ኮንፍረንሱን በንግግር የከፈቱት የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው ምርጫ የአንድ አገር የሉአላዊነት መገለጫ መሆኑን አንስተው ለጋሽ አገራት የምርቻ ሒደቱን ከመደገፍ ባሻገር በአገራዊ ጉዳይ ላይ እጃቸውን እንዳያስገቡ አሳስበዋል። በኮንፍረንሱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሰብኣዊ መብት ተማጋቾች፣ የሚዲያ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here