0
1596

በመዲናዋ ለአንድ ወር የሚቆይ ነፃ የኤሌክትሪክ ታክሲ አገልግሎት በተመረጡ 6 አቅጣጫዎች መሰጠት ተጀመረ

ሐምሌ 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ግሪን ትራንስፖርት ሰርቪስ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የትራንስፖርት እንግልትን ትኩረት በመስጠት ከትራንስፖርት አና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአንድ ወር የሚቆይ የ “ጎ ግሪን” የታክሲ አገልግሎትን በተመረጡ 6 አቅጣጫዎች መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

በትናንትናው ዕለት ለተጀመረው ለዚህ ነፃ የትራንስፖር አገልግሎትም 60 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሰማራታቸው ተነግሯል።

የጎ ግሪን ታክሲዎች ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ፤ የነጻ የታክሲ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ የመዲናችን ነዋሪዎች “ጎ ግሪን አፍሪካ” የሚለውን መተግበሪያ ስልካቸው ላይ በመጫን እና በመጠቀም አገልግሎቱን ማገኘት ይችላሉ ተብሏል።

የጎ ግሪን ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መሰመሮች

1. ከስታድየም በደምበል ወደ ቦሌ መስመር

2. ከመገናኛ አያት አደባባይ መስመር

3. ከፒያሳ ብሄራዊ ሜክሲኮ መስመር

4. ከፒያሳ አራት ኪሎ መገናኛ መስመር

5. ከአደይ አበባ ወደ ስቴድየም መስመር

6. ከስታድየም ልደታ ጦር ሃይሎች መስመር ሲሆኑ፤ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከጠዋት አንድ ሰዓት እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ ይሰጣል ተብሏል።

ግሪን ትራንስፖርት ሰርቪስ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለትራንስፖርት ዘርፍ በማሰማራት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በመተግበርያ እና በጥሪ ማዕከል የሚከናወን የሜትር ታክሲ አገልግሎት ይሰጣል። የትራንስፖርት አገልግሎቱም “ጎ ግሪን አፍሪካ “ተብሎ ይጠራል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here