የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያዋ 10 ሺህ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ መያዟ ተገለጸ

0
838

ዕረቡ ሐምሌ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የጉለሌ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነችው ግለሰብ 10 ሺህ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ መያዟን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የአንድን ባለጉዳይ ጉዳዩን እኔ እጨርስልሀለሁ በማለት 10ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የግል ተበዳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከድንበር ጋር የተያያዘ ጉዳዩን ለማስጨረስ በሄደበት አጋጣሚ ግለሰቧ 30 ሺህ ብር ጉቦ የጠየቀችው ሲሆን፤ 10 ሺህ ብር ቅድሚያ እንደሰጣት እና ቀሪውን 20 ሺህ ብር ጉዳዩ ሲያልቅ ለመወሰድ መጠየቋን የግል ተበዳይ ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ገልጸዋል።

ሐምሌ 8 ቀን 2014 ጉቦውን ስትቀበል በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት ነው የተገለጸው።

ማህበረሰቡ መሰል ወንጀል ፈፃሚዎችን ለህግ አካል አጋልጦ የመስጠት ልምዱ ይበል የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፤ ወደፊትም ህዝብን እና መንግስትን የሰጣቸውን እምነት በማጉደል በማህበረሰቡ ላይ በደል የሚፈጽሙ አካላትን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here