ሦስተኛው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ወደ ኢትዮጵያ ተላከ

0
1178

የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ በተከሰተው የፋብሪካዎች መዘጋት ምክንያት ተጓትቶ የነበረው ሦስተኛው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን መገጣጠም ተጠናቆ በቂ ፍተሻ ከተደረገበት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል።

በኢትዮጵያ መርከቦች ድርጅት ትብብር፣ በመርከብ ወደ ጂቡቲ ወደብ ጉዞ የጀመረ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ማሽኑ ለአማራ ክልል መንግሥት የጣና እና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በነጻ የተበረከተ መሆኑም ተመላክቷል።

ማሽኑ ባለ 80 የፈረስ ጉልበት የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ 27 ነጥብ 5 ኪዩቢክ ሜትር መያዝ የሚችል በመሆኑ፣ በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን እንቦጭ ለማስወገድ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

ወጪው የተሸፈነው በዋሽንግተን ዲሲ፣ በዳላስ፣ በችካጎ እና በእንግሊዝ በተደረጉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ ገንዘባቸውን በለገሱ ኢትዮጵያዊያን ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ኹለት የእንቦጭ ማጨጃ ማሽኖች ለክልሉ መለገሳቸው ይታወሳል።


ቅጽ 4 ቁጥር 194 ሐምሌ 16 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here