መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናአዲሱ በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ አቀረቡ

አዲሱ በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ አቀረቡ

ሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ዶ/ር ፋሃድ ኦባይዳላህ አልሁማየዳኒ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ዛሬ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ደመቀ አጥናፉ አቅርበዋል።

ደመቀ አጥናፉ የሹመት ደብዳቤውን በተቀበሉበት ወቅት፤ ለአምባሳደሩ አዲስ ሹመት እንኳን ደስ አልዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈው፤ ባለፉት ዘመናት በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር የጸናውን የኹለቱን አገሮች ታሪካዊ ግንኙነት አድንቀዋል።

በመቀጠልም አገራቱ የኹለትዮሽ ግንኙነታቸውና አጋርነታቸን ጠንካራ መሰረት የተጣለው በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የነብዩ መሀመድ ተከታዮችን ተቀብላ ባስተናገደችበት ወቅት እንደሆነ አስታውሰዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አዲስ ለተሾሙት አምባሳደር በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ስላለው እርምጃም ገለፃ አድርገዋል።

በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ደመቀ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም በኹለቱ አገራት መካከል ስለሚደረግ የኹለትዮሽ ትብብር በተለይም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በልማት ፋይናንስ እንዲሁም የሰራተኛ ስምምነትን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ተለዋውጠዋል።

በመጨረሻም የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር በኹለቱ አገራት መካከል ያለው የኹለትዮሽ ግንኙነት እንዲጠናከር ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ሣሚ ጃሚል አብዱላህን ባሳለፍነው መጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ማሰናበታቸው ይታወሳል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች