ኖኪያ የ4G እና 5G ቴሌኮም አገልግሎት ለመዘርጋት አስቧል

0
835

ኖኪያ ከአዲስ አበባ ሳይንስና የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የዲጂታል ክህሎትንና የፈጠራ አቅምን ለማጎልበት እና በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርሟል።

የ4G እና 5G የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት መዘጋጀቱን የገለፀው ኩባንያው ለሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ አለም የደረሰበትን አሰራር እና የቴክኖሎጂ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የትምህርት እና ስልጠና ፕሮግራሞችንና የልምድ ልውውጦችን ማዘጋጀትን ስምምነቱ እንደሚያካትት ተገልጿል።

በፊርማዉ ስነ-ስርዓትም የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን በመወከል ኢሳያስ ገብረዩሀንሰ (ዶ/ር) እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅና ምእራብ አፍሪካ የኖኪያ ተጠሪ ዳንኤል ጃገር ፈርመውታል።

ኖኪያ በ1865 በፊንላንዷ ሔልንሲኪ ከተማ የተመሰረተ የቴክኖሎጂ ተቋም ሲሆን በ2018 የተቋሙ መረጃ መሰረት 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን በላይ ተገልጋዮች እና 22 ነጥብ 56 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዲሁም  ከ103 ሺሕ 083 በላይ ሰራተኞች ያሉት ተቋም ነው።
ኩባንያው የ4G እና 5G የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት መዘጋጀቱን ገለጧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here