መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ለአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ገፅታን ይዞ መጥቷል የተባለለት የሳርቤት – ጎፋ ማዞርያ – የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአግልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡

በከተማዋ የመንገድ ታሪክ የመጀመሪያው ነው የተባለለትና ረጅም ዋሻ ያለው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት፤ ከአሌክሳደር ፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ማሳለጫ ድረስ 3 ነጥብ 8 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ30-45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት ኖሮት የተገነባ መሆኑ ተነግሯል።

መንገዱ የፈጣን አውቶቢስ መንገድን ጨምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሸከርካሪዎችን በተመሳሳይ ጊዜ ሊያሳልፍ በሚያስችል ስፋት ከመገንባቱም በላይ፤ 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ እና ከመሬት ከፍ ብሎ የተገነባ ረጅም ማሳለጫ ድልድይ እንዳለውም ተገልጿል።

ግንባታው በ2012 የተጀመረው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት መጠናቀቁ፤ ከመንገድነቱም ባሻገር የአካባቢውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ከባቢያዊ ገፅታ በእጅጉ የቀየረ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለመንገድ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ በጀት በመመደብ በርካታ መንገዶችን ግንባታ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጾ፤ አሁንም ይህንን አጠናክሮ በመቀጠል ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን መስራቱን እንደሚቀጥልም ገልጿል።

በመንገድ ፕሮጀክቱ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የቻይና ኤምባሲ ቻርጅ ዲ አፌርስ ሺን ኪንግማን፣ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ጃንጥራር አባይ እንዲሁም የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተውበታል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች