”በ2015 በጀት ዓመት አስተማማኝና ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል ለመገንባት እየሰራን ነው።“:- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

0
1651

ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በ2015 በጀት ዓመት ለሰራዊታችን የተሟላ ሎጂስቲስቲክስ በማቅረብ አስተማማኝና ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል ለመገንባት እየሰራን ነው ሲሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ከኹሉም ዕዞች ከተውጣጡ የሎጂስቲክስ አመራሮች ጋር ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀምን በመገምገም ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፃ አቅርበዋል።

የሎጀስቲክስ አቅርቦት የሰራዊቱ የጀርባ አጥንት መሆኑን የጠቀሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በኹሉም አቅጣጫ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን ግምባር ፈጥረው ቢሰለፉም ለሰራዊታችን የተቀናጀ ሎጂስቲካዊ ፍላጎቶችን በማቅረብ ከሰራዊቱ ጀግንነት ጋር ተዳምሮ ጠላትን ማሳፈር ችለናል ብለዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ሰራዊቱ ዘመኑ ያፈራቸውን ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን እናስታጥቃለን ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የሎጂስቲክስ አሰራር እና ሥርዓት በሚፈቅደው ልክ ሰራዊቱ በሚያስፈልገው ቦታ እና ሰዓት የሚያስፈልገውን ኹሉ በማቅረብ ሎጂስቲክስ የሰራዊቱ ደጀን መሆኑን ገልጿል ብለዋል።

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌ/ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል በበኩላቸው፤ የሎጂስቲክስ ዝግጁነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ያደገ መሆኑን መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here