ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ ተላለፈ

0
2908

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል

ማክሰኞ ነሐሴ 10 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ትምህርት ሚኒስቴር ኹሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የ2015 የትምህርት ካላንደራቸው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ የሚሰጠውን የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ታሳቢ ያደረገ መሆን እንደሚገባው ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 በኹሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ እና ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እና የምግብ አቅርቦት ዝግጅት እንዲደረግም ትዕዛዝ ተላልፏል።

ከፈተና ደህንነት እና አቅርቦት ጋር በተያያዘ የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የሚመራ ዋና ግብረ ሃይል እንዲሁም በየካምፓሶቹ ካምፓስ ሃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ ሃይል እንዲደራጅ መመሪያ መተላለፉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here