መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል በሚል ምክንያት የሦስት ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት...

ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል በሚል ምክንያት የሦስት ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የገደለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣች

ማክሰኞ ነሐሴ 10 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል በሚል ምክንያት የሦስት ልጆቿን አባት በመጥረቢያ በመምታት የገደለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ትዕግስት አዘዘው የተባለቸው ግለሰብ ወንጀሉን የፈፀመችው መስከረም 10 ቀን 2014 በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አንቆርጫ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሿ በዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የ3 ልጆቿ አባት የሆነው ባለቤቷን ሟች አወቀ ይርዳውን “ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ጀምረሃል፤የተለያዩ ሴቶችንም በስልክ ታናግራለህ” በሚል ምክንያት ሶፋ ላይ በተኛበት ጭንቅላቱን በመጥረቢያ ደጋግማ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጓን በአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ከሰው መግደል ወንጀል ምርመራ ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ግለሰቧ በፈፀመችው ወንጀል በቁጥጥር ሥር ውላ ምርመራ ከተጣራባት እና ክስ ከተመሰረተባት በሗላ፤ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የከባድ ውንብድና እና ግድያ 1ኛ ወንጀል ችሎት በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ጥፋተኛ መሆኗን በማረጋገጥ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች