በአዲስ አበባ ሰባት የንግድ ማዕከላት ሊገነቡ ነው

0
1152

በአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በአዲስ አበባ በኹሉም በሮች ሰባት የንግድ ማዕከላት ሊገነቡ እንደሆነ የኢፌዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። መንግስት በድጎማ በርካታ ምግብ ነክ ነገሮችን በማቅረብ ለዝቅተኛው የሕብረተሰብ ክፍል በማዳረስ ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው። በዚህም መሰረት አዲስ የሚገነቡት የንግድ ማዕከላትም ተደራሽነቱን በማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ እሸቴ አስፋው እንደተናገሩት መንግስት  በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በኅብረት ስራዎች ኮርፖሬሽን ፣በኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት፣ በኅብረት ስራ ኤጀንሲ እና በሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበራት አማካኝነት ለኅብረተሰቡ እያቀረበ ያለውን ምርቶችን በስፋት ለማዳረስ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።

መንግስት በድጎማ ከሚያቀርባቸው ምርቶች በተጨማሪም ሽንኩርት፣ ድንች፣ በርበሬና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎችን ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ደግሞ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተስፋ ብርሃን ሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ ጌታሁን ደስታ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here