ዜና ዕረፍት

0
629

በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ1997 ጀምሮ በአባልነት ሲያገለግሉ የነበሩት ክብርት አየኋት አሰፋ ቸኮል ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በአማራ ክልላዊ መንግስት በ1962 አብምሴ ሳርምድር ወረዳ የተወለዱት አየኋት የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአብርሃ ወአፅብሀ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በስራ አመራርም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ከ1997 ጀምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ሕዝብን ማገልገል ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የቋሚ ኮሚቴዎች በአባልነት አያገለገሉ ሲሆን ህይወታቸው እስካለፈበት ድረስም በተፈጥሮ ሃብት፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአባልነት በማገልገል ላይ እንደነበሩ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል። አየኋት ባለትዳርና የኹለት ወንድ ልጆች እናት ሲሆኑ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 7/2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ስነ ስርዓታቸውም በትውልድ ቀያቸው ጎጃም መርጦ ለማሪያም ጥቅምት 8/2012 እንደሚፈፀም ታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በክብርት አየኋት ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here