”ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ የሚመለከታቸው ሰራተኞች ከሥራ ታግደዋል”:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

0
1301

አርብ ነሐሴ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቁጥር ET343 አውሮፕላን ከአዲስ አበባ አየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ጋር ያለው ግንኙነት በጊዜያዊነት መቆራረጡን የሚያመላክት ዘገባ እንደደረሰው ገልጾ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሰራተኞችን ከሥራ ማገዱን አስታወቀ።

ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2014 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET343 ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ በጉዞ ላይ እያለ ኹለቱም አውሮፕላን አብራሪዎች በበረራ ላይ በድንገት እንቅልፍ እንደጣላቸው አቪዬሽን ሄራልድ ዘግቧል።

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ከአብራሪዎች ጋር ለመገናኘት በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው እንደቀረና፤ የአውሮፕላኑ አውቶ ፓይለት ሲስተም ሥራውን ሲያቋርጥ ባሰማው የማንቂያ ድምጽ ምክንያት አብራሪዎቹ በመንቃት ከመድረሻ ሰዓታቸው 25 ደቂቃ ዘግይተው አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ መድረሳቸውን ኤር ላይቭ አቪዬሽን ሄርልድን በዋቢነት ጠቅሶ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የተቋረጠው ግንኙነት ከተስተካከለ በኋላ አውሮኘላኑ በሰላም ማረፉን የገለጸ ሲሆን፤ ”በምርመራው ውጤት መሰረት ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል” ብሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here