ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከሰሞኑ አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ወርቅ ቤት ገዢ መስለው በተደራጀ መልኩ ወርቅ ሲሰርቁ በካሜራ እይታ ውስጥ የገቡትን ዘራፊዎች በጥብቅ እንደሚፈልግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የተጠርጣሪዎቹን አድራሻ የሚያውቅ አልያም በአጋጣሚ የተመለከተ ማንኛውም ገሰለሰብ በ 0115309139 ዘውትር በሥራ ሰዓት ከ2:30 – 11:30 እንዲሁም በ0111119475 / 0111711012 በማንኛውም ሰዓት ደውሎ እንዲያሳውቅ ፖሊስ ጠይቋል።
በተጨማሪም በነፃ የስልክ መስመር 861 መጠቀምም እንደሚቻል ፖሊስ ገልጿል።
በወንጀል ተጠርጣሪዎቹ ከላይ በፎቶ እና በቪዲዮ ምስል የሚታዩት ሲሆኑ፤ ከመካከላቸው የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሰ ግለሰብ ይገኝበታል።



