ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሻደይ በዓል በአማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።


በዓሉ በየዓመቱ በወርሀ ነሐሴ የሚከበር ሲሆን፤ የነፃነት፣ የእኩልነትና የአንድነት ማሳያ ተደርጎ የሚታይና፤ በተለይም ሴት ወጣቶች የሻደይን ጨዋታ እየተጫወቱ የሚያከብሩት በዓል መሆኑ ይታወቃል።



