የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ከ20 በላይ ለሚሆኑ ጀኔራሎች ለእያንዳንዳቸው 150 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ አበረከተ

0
1273

ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የህልውና ዘመቻውን ከፊት እየመሩ ድል ላስመዘገቡ ከ20 በላይ ለሚሆኑ ጀኔራሎች ለእያንዳንዳቸው 150 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ አበርክቷል።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ መላሽ ወርቃለም እንደገለፁት፤ የአባቶቻችንን ታሪክ ለደገሙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የከተማችን ህዝብና ከተማ አስተዳደራችን የህልውና ዘመቻውን ከፊት ሁነው ለመሩ የአገራችን ጀግኖች ጀነራሎች፤ ትንሽም ብትሆን በሥማቸው ሊጠራ የሚችል ከሀያ በላይ ለሚሆኑ ጀነራሎች ለእያንዳንዳቸው 150 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ሰጥተናል ብለዋል።

ምክትል ከንቲባው ጀኔራሎቹ ስላደረጉት ተጋድሎ በከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ሥም ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ ለጄኔራል አበባው ታደሰ፣ ለሌ/ጀነራል ዘውዱ በላይ፣ ለጄኔራል በላይ ስዩም፣ ለጀነራል አሰፋ ቸኮለ፣ ለሌ/ጀነራል ደሳለኝ ተሾመ፣ ለጀነራል ሰሎሞን ኢተፋ፣ ለሜ/ጀነራል ሙሉአለም አድማሱ እና ለሌሎች ጀነራሎች በስጦታ መልክ ቦታው መበርከቱን መናገራቸውን ከዋግ ኸምራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here