የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ወታደራዊ መለዮ ልብስ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረት መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።
በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ኩባንያው ዩኒፎርሞቹን ከኹለት ሳምንት በፊት ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ በምርት ሂደቱ ላይ ባሉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ከ177 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ሥራውን የጀመረው ኩባንያው፣ አሁን ላይ የጨርቃ ጨርቅ ዘርፉ ላይ በመሰማራት ከ2 ሺሕ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉ ተጠቅሷል።
ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ደግሞ በአሁን ሰዓት ከ20 በላይ አምራች ኩባንያዎችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ካሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ቀደምት ከሚባሉት የሚጠቀስ መሆኑ ተመላክቷል።
ቅጽ 4 ቁጥር 200 ነሐሴ 28 2014


