መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ...

በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለጸ

በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርትም ከኹሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሙከራ ትግበራ እንደሚጀምርም ገልጿል።

አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሙከራ ትግበራ ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራንም ሥርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ሥልጠና መሰጠቱን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ሥራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልጸዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ትምህርት በይፋ እንደሚጀመርም በመግለጽ፤ ለዚህም የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉን አስረድተዋል።

የዳይሬክቶሬሩ ሥራ አስፈጻሚ አክለውም፤ በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ስርዓት እንደሚያካሄድ የገለጹ ሲሆን፤ ተማሪዎች ደስ ብሏቸው የትምህርት ቀኑን እንዲጀምሩ በየትምህርት ቤቶቹ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱም ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ በክልል ያሉ ትምህርት ቢሮዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ድርጅቶች በትምህርት ቤት ውስጥ መዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅተው ተማሪዎችን የመቀበል ሥነ ስርዓት እንደሚያካሄዱም አስረድተዋል።

ለዚህም ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ መምህራን እና የማህበረሰቡ ክፍል ጋረሰ በትምህርቱ የጊዜ ሰሌዳ እና በሥርዓተ ትምህርቱ አፈጻጸም ላይ ውይይቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በየክልሎቹ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም የመማር ማስተማር ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያስረዱት አመለወርቅ፣ በዚህም የትምህርት ቤቶች እድሳት፣ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመጽሐፍት ማስተዋወቅ እና የትምህርት ጉባዔ የማካሄድ ሥራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 202 መስከረም 7 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች