በጃዋር መሐመድ ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳልተወሰደ ተገለፀ

0
524

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአክቲቪስት ጃዋር መሐመድ ላይ ምንም አይነት በመንግስትም ሆነ በፖሊስ በኩል እርምጃ እንዳልተወሰደ አስታወቀ። የፌደራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ጥቅምት 12/2012 በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በጃዋር መሐመድ በኩል ጥቃት ሊደርስበት እንደሆነ በማስመሰል ጥሪ ያቀረበው ከእውነት የራቀ እና ምንም አይነት እርምጃ እንዳልተወሰደ ገልፀዋል። ግለሰቡም ጤናማ በሆነ ሁኔታ የዕለት ተዕለት ስራቸውን እያከናወኑ እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

ኮሚሽሩ አያይዘውም በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ ወደ አገር ውስጥ ገቡ ሰዎችን መንግስት በሚኖሩበትና በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ የጥበቃ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው፤ በአሁኑ ሰዓት እየታየ የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ምክንያት ባድረግ ጥበቃዎችን የማንሳት ስራ መንግስት እየሰራ እንደሆነም አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት የጃዋር ጥበቃዎችን የማንሳት ስራ መንግስት መስራቱንም አስታውቀዋል። ፌደራል ፖሊስ ጨምሮ እንደገለፀው፤ ኅብረተሰቡ ምንም መረበሽ ሳያሻው ዕለት ተዕለት ስራውን ማከናወን እንደሚገባው እና ከፖሊስ ጋርም በመተባበር ሰላሙን እንዲያስጠብቅ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ ጥቅምት 12/2012 ከማለዳ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች አለመረጋጋት የተከሰተ ሲሆን መንገዶችም ዝግ መሆናቸውን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here