ዕረቡ መስከረም 11 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ምርመራ ምክትል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ክንዱ ወንዴ በሰጡት መግለጫ፤ ዘመነ ካሴ በኅብረተሰቡ ጥቆማ በሕግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተካሔደበት ነው ብለዋል።
በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከግለሰብ ቤት መያዙን ገልጸዋል።የወንጀል ተጠርጣሪው በሕግ ቁጥጥር ሲውል 541 ሺህ ብር እና ከሌሎች ኤግዚቢቶች ጋር መያዙን ተናግረዋል።
ምርመራው የሚካሔደው በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን ማረጋገጣቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ኮማንደር ክንዱ ተጠርጣሪው በሕግ ሲፈለግ እንደቆየ ገልጸው እንዲያዝ ለተባበረው ማኅበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።
ማንም ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል የተጠርጣሪው መያዝ ማሳያ ነው ብለዋል።