መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለራቁ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪ እንደሚሸፈን ተገለጸ

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለራቁ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪ እንደሚሸፈን ተገለጸ

አርብ መስከረም 13 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆነ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ ተገለጸ፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 በኹለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም ፈተና ማተምን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ መጠናቀቃቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ለኤፍ ቢ ሲ ተናግረዋል።

ትራንስፖርትን በተመለከትም ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች ወጪን በራሳቸው እንደሚሸፍኑም ተገልጿል።

ሆኖም ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚያመቻቹም ተጠቁሟል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች