መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 የዘውዳዊ ስርዓት ያላቸው የአውሮፓ አገራት

10 የዘውዳዊ ስርዓት ያላቸው የአውሮፓ አገራት

ምንጭ፡-ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው (2022)

የኢንግሊዟ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤት ማረፋቸውን ተከትሎ፣ ‹ዘውዳዊ ስርዓት አሁንም አለ እንዴ?› ብለው የጠየቁ ብዙዎች ናቸው። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የዓለም አገራት በታሪካቸው ዘውዳዊ ስርዓት ያላቸው ናቸው። ታድያ ያ ስርዓት ‹ባህላዊ› ወይም ‹ኋላቀር› ተብሎ ሲቀየር፣ አንዳንዶቹ አገራት ስርዓቱ በታሪክ መዛግብት ላይ ብቻ ሰፍሮ የሚቀመጥ ሳይሆን በአካልም የሚገኝና የሚታይ፣ በአገር ጉዳይም እንደ ወትሮም ባይሆን እንኳ የራሱ ድርሻና ሥራ ያለው ሆኖ እንዲቀመጥ አድርገዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት ንጉሣዊ ስርዓትን ከታሪክ ሳይቀር ለመፋቅ ደፋ ቀና የሚሉ በሚመስሉበት በአሁን ወቅት፣ በዓለማችን 26 የሚሆኑ ንጉሣዊ ስርዓት ያለባቸው አገራት ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል ደግሞ 12 የሚሆኑት በአውሮፓ የሚገኙ ናቸው። የተቀሩት ደግሞ በአፍሪካ እንዲሁም በእስያ እና በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የሚገኙ ናቸው።


ቅጽ 4 ቁጥር 203 መስከረም 14 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች