መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናከስደት በተለያየ ግዜ ወደ ሐገር ቤት ከገቡ ሴቶች መካከል የተወሰኑት በሴተኛ አዳሪ...

ከስደት በተለያየ ግዜ ወደ ሐገር ቤት ከገቡ ሴቶች መካከል የተወሰኑት በሴተኛ አዳሪ ህይወት ውስጥ እንደሚገቡ በጥናት መረገጋጡ ተነገረ

ዕረቡ መስከረም 18 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተደረገ ጥናት ከስደት በተለያየ ግዜ ወደ ሐገር ቤት ከገቡ ሴቶች መካከል የተወሰኑት በሴተኛ አዳሪ ህይወት ውስጥ እንደሚገቡ መረጋገጡ ተነግሯል።

አብዛኛው ወደዚህ ህይወት የገቡ ሴቶች ከሥራው መውጣት እንደማይፈልጉም ተመልክቷል።

የክፍለ ከተማው የሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ንጋቱ ጥላሁን እንደተናገሩት የናሙና ጥናቱ በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩ ከ160 በላይ ሴቶች ዳሷል።

ከዚሁ ሥራ ለማስወጣት የሥራ እድልና አጫጭር ሥልጠና ለመስጠት ቃል መጠይቅ የተደረገላቸው ሴቶች፣ ከሴተኛ አዳሪነት ለመውጣት ፍላጎት እንደሌላቸው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ከተለያዩ የአረብ ሐገሮች የመጡ ሴቶች ሲጠየቁ በቀን ከዚሁ ሥራ ከ2000 ብር በላይ እንደሚያገኙ መናገራቸው ተገልጿል።

ይህንን ለማስቀረት፣ ወደዚህ ህይወት እንዳይገቡና እንዳይቸገሩ ለማድረግ፣ ከስደት የተመለሱ ሴቶች የአለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ‘IOM’ እና ከሚመለከታቸው ጋር ሴቶቹን እያሰለጠኑ ነው።

በየግዜው ከስደት የሚመለሱ ሴቶች፣ ከበጀት እጥረትና ከግብረሰናይ እርዳታ ማጠር ምክንያት እራሳቸውን እንዲለውጡ ማድረግ ፈተና ሆኗል ተብሏል፡፡

ወሬውን የተሰማው ዛሬ፣ በ ‘IOM’ የገንዘብ ድጋፍ በተገኘ ወጪ የተወሰኑ የስደት ተመላሾች፣ በሐገራቸው በተለያየ ሙያ ሠልጥነው፣ ውለው እንዲገቡ ለማድረግ የተሠራው በቀረበበት ፕሮግራም ላይ መሆኑን ሸገር 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ከስደት የተመለሱ ሴቶች ወደ ሐገር ሲገቡ በጣም ተጎድተው እንደሚመጡና ከሚመለከታቸው ጋር ሆኖ የሚያሰለጥነው “እሹሩሩ” የተባለ ድርጅት በጀት ይዞ አቅም የሌላቸውንም እንደሚያሰለጥንም ተገልጿል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች