ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂ አስተዋወቀ

0
672

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂ እና የ2015 በጀት ዓመት የሥራ እቅዱን በዛሬው እለት አስተዋውቋል።

ከ2011 እስከ 2014 የቆየው ‹ብሪጅ/ድልድይ› የተሰኘው ስትራቴጂ ኩባንያው ብቁ፣ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የቴሌኮም ኦፕሬተር እንዲሆን መሠረት የጣለ እንደነበር ኩባንያው ገልጿል።

ኩባንያው በሦስት ዓመት ውስጥ የደንበኞችን ቁጥር ከ37 ሚሊዮን ወደ 66 ሚሊዮን ማሳደግ ችሏል የተባለ ሲሆን፣ በሦስት ዓመት ውስጥ ገቢውን 76 በመቶ ማሳደጉንና የውጪ ምንዛሪ 104 በመቶ እድገት ማስመዝገቡም ነው የተመላከተው።

ሊድ የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም አዲሱ የሦስት ዓመት እቅድ ስትራቴጂ ከሐምሌ 2014 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። ስትራቴጂው በቀጣይ ሦስት ዓመት አስተማማኝ የኮምዩኒኬሽን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ ሕይወትን ማቅለል እና የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማፍጠን ላይ በትኩረት ይሠራል ነው የተባለው።

በቴሌኮም ገበያ ከፍተኛ ድርሻ በመያዝ እና የደንበኞቹን የአገልግሎት እርካታ በማሳደግ ብሎም የአገልግሎት ተደራሽነት ማስፋት ላይ እንደሚሠራም ተጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 204 መስከረም 21 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here