የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ 10 ተንቀሳቃሽ የሕክምና ክሊኒኮች ድጋፍ ማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ።
የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር ተፈራርመዋል።
በድጋፍ ስምምነቱ መሠረትም የጃፓን መንግሥት 185 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 10 ተንቀሳቃሽ የሕክምና ክሊኒኮችን እንደሚያበረክት ተገልጿል። ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮቹ ሙሉ የሕክምና አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎችን የሚያሟሉ መሆናቸው ተመላክቷል።
ክሊኒኮቹ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለሚገኙ አርብቶ አደሮች እና በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውም ተጠቁሟል።
ቅጽ 4 ቁጥር 204 መስከረም 21 2015


