ኢትዮጵያ የዓለም ዐቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች

0
619

ኢትዮጵያ በካናዳ ሞንትሪያል በተካሄደው 41ኛው ስብሰባ ላይ የዓለም ዐቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች።

ኢትዮጵያን በመወከል ከኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር የተወከለ የልዑክ ቡድን ተሳትፎ አድርጓል።

በዚህም ኢትዮጵያ በካናዳ ሞንትሪያል በመካሄድ ላይ በሚገኘው 41ኛው የዓለም ዐቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በከፍተኛ ድምጽ የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧን ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧ በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን የላቀ ውጤት የሚያመላክት ነውም ተብሏል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ወደብ አልባ አገር በመሆኗ የተነሳ ከውጪው ዓለም ጋር ለመገናኘት የምትጠቀመውን የአየር ትራንስፖርት በተመለከተ በድርጅቱ የሚተላለፉ ማንኛውንም ውሳኔዎች በቅርብ በመከታተል ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር እንደሚረዳ ታምኖበታል።

በዓለም ላይ በአቪዬሽን ዘርፍ ከፍተኛ ሥምና ዝናን ያተረፉ 36 አገራት አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ኢትዮጵያ ከ1936 ጀምሮ የዓለም ዐቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት መሥራችና የዓለም ዐቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ኮንቬንሽን ፈራሚ ከሆኑ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ መሆኗም ተመላክቷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 205 መስከረም 28 2015

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here