የእጅ መንሻ ሲቀበል የነበረው ፖሊስ ዕጅ ከፍንጅ ተያዘ

0
612

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ይርጋ ኃይሌ የገበያ ማዕከል ሦስተኛ ፎቅ በሚገኘው ሉሲ ካፌ ውስጥ 3መቶ ሽሕ ብር ጉቦ ሲቀበል የነበረው ፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የገቢዎችና ጉምሩክ ኢንተለጀንስ ሰራተኛ መሆኑንም ገልጿል። አያይዞም ግለሰቡ የማይገባው ጥቅም ለማግኘት ሲል ግብር ከፋይና የግል ተበዳይ ከሆነች ግለሰብ የ300ሽሕ ብር ጉቦ ሲቀበል በፖሊስ አባላት መያዙን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ ገልጸዋል።

የጉዳዩ መርማሪ የሆኑት ኢ/ር ጎይቶም ሃለፎም እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲል የግል ተበዳይን የ2007 እና የ2008 የግብር ደረሰኝ የከፈለችበት ስህተት ስላለበት ይህ ደግሞ በወንጀል ስለሚያስጠይቅሽ እኔ ላስተካከልልሽ እችላሉ በማለት ከቀጠራት በኋላ ጥቅምት 15/ 2012  ይዛለት የመጣችውን ገንዘብ ተቀብሎ ለመሄድ ሲሞክር በፖሊስ አባላት ከ3 መቶ ሺ ብር ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ጉዳዩ በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here