ሞባይል ጠጋኙ ግለሰብ የ20 ሚሊዮን ብር አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ

0
1082

ማክሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ነዋሪነቱ አዲስ አበባ የሆነው ማትያስ ግርማ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊዮን ብር አሸናፊ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ “በሞባይ ጥገና የሚተዳደሩት የ40 ዓመቱ የ20 ሚሊዮን ብሩ ዕድለኛ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ወረዳ 11 ነዋሪ ናቸው” ብለዋል፡፡ላለፉት 30 ያህል ቀናት እድለኛው ሲፈለግ የነበረ ሲሆን፤ አሁን አሸናፊው መረጋገጡን ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው፡፡

ከዚህ በፊትም አስተዳደሩ ለመጀመርያ ጊዜ የ20 ሚሊዮን ብር የእድል ቁጥር ባዘጋጀበት ጊዜም አሸናፊው የታወቀው እጣው ከሚያበቃበት ስድስት ወራት ውስጥ በመጨረሻዎቹ አምስት ቀናት ላይ ነበር፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here