ማክሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በብሄራዊ ደረጃ የሚከበረውን የአገር መከላከያ ሠራዊት ቀን “ስለተሰዋልን ደም እና አጥንት ፣ስለተከፈለልን ህይወት፣ ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘው በፓሽን አካዳሚ እየተከበረ ነው።
በዓሉ የቀድሞው የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራር የነበሩት ብርጋዴል ጀኔራል ካሳየ ጨመዳን ጨምሮ የአካዳሚው ሰራተኞች፣ተማሪዎች ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
በመርሃግብሩ ላይ የነገ አገር ተረካቢ ትውልዱ የአገርን ፍቅር እንዲረዳ መከላከያ ሰራዊት እየከፈለ ያለውን መስዕዋትነት እና የህይወት ተጋድሎ ክብር መስጠት ያስፈልጋል። ለዚህም መምህራን ሀላፊነት አለባቸው መባሉን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።
የአገር መከላከያ ሠራዊት ቀን “ህዝባችን የጥንካሬያችን ምንጭ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ቀን እንደሚከበር መገለፁ ይታወቃል።



