ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

0
549

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክል ፖምፒዮ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ እና ስለ ቀጠናው ኹኔታ በስልክ ተወያዩ። ፖምፒዮ በቅርቡ በኦሮሚያ የተከሰተውን ዘርን መሰረት ያደረገ ግጭት በተገቢው መንገድ እና በሰላማዊ አካሔድ መፈታት እንደሚኖርበት ምክራቸውን አስቀምጠዋል።

የኹለቱን አገራት ጠንካራ ግንኙነት ጠቀሜታ ያሰመሩበት ፖምፒዮ በኢትዮጵያ የተካሔደውን ታሪካዊ ለውጥም አገራቸው አሜሪካ እንደምትደግፍ አስታውቀዋል። ስለ ቀጠናው ነባራዊ ሁኔታ የተወያዩት ኹለቱ ወገኖች ከአሜሪካ ወገን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የደቡብ ሱዳንን ጉዳይ በሚመለከት በማደራደር ፣ ብሔራዊ አንድነትን በመተግበር እና ዘላቂ ሰላም በማምጣት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ሃሳብ አቅርበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here