በ10 አመታት 20 ሚሊዮን የስራ እድል ለመፍጠር የሚያሰችል ዕቅድ ይፋ ተደረገ

0
611

በኢትየጵያ 70 ከመቶ የሚደርሰው ህዝብ እድሜው ከ30 ዓመት በታች የሆነ ወጣት መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀጣይ አመታት 20 ሚሊዮን የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ዕቅድ በስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ይፋ ተደረገ።

በእቅዱ መሰረትም መንግስት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማትን የሚደግፈበትን መንገድ እንደገና በማጤን ለውጥ በማድረግ፣ ንግድ በመጀመር ሂደት ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም ላይ በትኩረት በመስራት ሚሊዮኖችን ባለስራ ለማድረግ ማሰቡን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የስራ አጥነት ምጣኔ 19 በመቶ የደረሰ ሲሆን እድሜያቸው ከ 15 እስከ 29 በሆኑ ወጣቶች ዘንድ ደግሞ 25 በመቶ ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪም ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት በየዓመቱ አምስት በመቶ በማደግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአገሪቱ በቀጣይ አምስት አመታት ስራ መስራት የሚችለውን ጎራ የሚቀላቀሉ ዜጎች ቁጥር በሚሊዮኖች እንደሚጨምር በእቅዱ ላይ ተተንብይዋል።
እነዚህን ስራ ፈላጊዎች ወደ ስራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለማየት፣ የስራ እድል የፈጠሩ ሰዎችን ልምድ ለማግኛት በማሰብ የስራ እድል ፈጠራን ከማበረታታት አንፃር ምን አይነት ፖሊሲ መቀረፅ አለበት፣ ስራ ፈጥረው ያሉ ሰዎች በምን መልኩ መደገፍ አለባቸው እና ችግሮቻቸውስ ምንድናቸው በሚሉ ጉዳዮች ላይ በሸራተን አዲስ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ላይም የግል ስራ ፈጣሪዎች በሀገሪቱ ያለው የብድር አቅረቦት አናሳ መሆን፣ የመንግስት የተንዛዛ ቢሮክራሲ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች እና የስልጠና ተቋማት በሙያቸው ብቁ የሆኑ ሰራተኞችን ማቅረብ አለመቻላቸው የግሉ ዘርፍ በርካታ ሰዎችን እንዳይቀጥር ማድረጉ ተገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 52 ጥቅምት 22 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here