አባ ዱላ ገመዳ ‹‹60 አመታት›› የተሰኘ አዲስ መጽሃፍ አስመረቁ

0
1007

የቀድሞው ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ 60 አመታት የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በማስመረቅ ከአንድ አመት ባነሰ ግዜ ሁለት መጽሃፍ ለገበያ ያቀረቡ ሲሆን አዲሱ መፅሃፋቸው በግል እና ፖለቲካዊ ሕይወታቸው ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ተገልጿል።

ከወራት በፊት የዳውን ሲንደሮም ህመም ተጠቂ በሆነች ልጃቸው የህይወት ታሪክ ላይ የሚያተኩር ዲቦራ የተሰኝ መፅሐፍ ‹‹ዲቦራ›› በሚል ርእስ ለአንባቢያን ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

በስራ ዘመናቸው የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስተሩ የደኅንነት አማካሪ በመሆን አገልግለዋል።
ከስራቸው በጡረታ በመገለልም በዳውን ሲንድረም ለተጠቁ ህፃናት የሚሰራ እና በልጃች ዲቦራ ስም የተሰየመ የበጎ አድራጎት ድርጅት አቋቁመው በመምራት ላይ ይገኛሉ። የአዲሱ መፅሐፍ ሙሉ ገቢም ለዚሁ በጎ አድራጎት ማህበር ማጠናከሪያ እንደሚውል ተገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 52 ጥቅምት 22 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here