ምንጭ፡-ተመድ (2021)
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በፈረንጆቹ 2021 የደን ሽፋናቸው በከፍተኛ መጠን የጨመሩ ብሎ ከዘረዘራቸው አገራት መካከል ቀዳሚዋ ቻይና ነች፡፡ ይህም 19 ሺሕ 370 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ስፋት ያለው ሲሆን፣ የለንደን ከተማን 12 እጥፍ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
አውስትራሊያና ህንድ ተከታዮቹ ሲሆኑ፣ ከአፍሪካ አገራት በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ የለም፡፡
በመንግሥታቱ ድርጅት እይታ የደን መጨፍጨፍ ሰው ሰራሽ ከሆኑ ችግሮች ውስጥ በጣም አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን፣ በዓመት 47 ሺሕ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ገደማ ስፋት ያለው መሬት በዚሁ ችግር ይራቆታል፡፡
ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥም ከአማዞን ጫካ 17 በመቶ ያህሉ ወድሟል፡፡
ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ አገሮች ደግሞ ተስፋ ሰጭ በሆነ መልኩ የደን ሽፋን መጠናቸውን እየሳደጉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ቅጽ 5 ቁጥር 210 ኅዳር 3 2015