መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየፓኪስታኑ ጂ ኤስ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ

የፓኪስታኑ ጂ ኤስ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ የቀረበለትን ግብዣ መቀበሉን አስታወቀ

ረቡዕ ኀዳር 14 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር አብዱላህ በፓኪስታን ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሀብቶች እና የቢዝነስ ሰዎች ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

አምባሰደሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ዘርፉን ለውጪ ባንኮች መክፈቱንና ሌሎች አዋጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን አስተዋውቀዋል፡፡ ፓኪስታን ኦብሰረቨር እንደዘገበው አምባሳደር ጀማል በከር ለፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ምርጡ ጊዜ አሁን ነው ብለዋል፡፡ከአምባሳደሩ ጋር ቆይታ ከአደረጉ የአገሪቱ የቢዝነስ ሰዎች መካከል ጃሃንጊር ሲዲቅ ይገኙበታል፡፡ ጃሃንጊር የፓኪስታኑ ጄ ኤስ ባንክ መሥራች ሲሆኑ የአምባሳደሩን ግብዣ መበላቸውን እና በቅርቡም የቢዝነስ ልዑካንን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ገልጸዋል፡፡

ጄ ኤስ ባንክ 812.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አሴት ያለው እና ዋና ጽ/ቤቱን በፓኪስታን ካራቺ አድርጎ በባህሬን እና በሌሎችም ሀገራት ዓለም አቀፍ ቅርንጫፎች ያሉት የፓኪስታን ግዙፍ የንግድ ባንክ ነው፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች