መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበምዕራብ ጎጃም ዞን በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን የተገነባ ቤተ ክርስቲያን በቁፋሮ መገኘቱ ተገለጸ

በምዕራብ ጎጃም ዞን በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን የተገነባ ቤተ ክርስቲያን በቁፋሮ መገኘቱ ተገለጸ

ረቡዕ ኀዳር 14 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን አቸፈር ወረዳ በፎረሄ ኢየሱስ ቀበሌ 702 ዓመታትን ያስቆጠረ ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም በተደረገ ቁፋሮ መገኘቱ ተነግሯል።

መልሶ የሚቋቋመው ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ሂሩት አምላክ እንደተመሰረተ የተገለፀ ሲሆን፤ ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ ተብሎ ይታወቃል።

የተገኘው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተገነባ የሚያረጋግጥ ብዕራና መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በታሪክ የተሰነዱ ማስረጃዎች ከእምነት አባቶች እንደተገኘ ተገልጿል። የቅዱሳን አፅም የያዘ ከኖራ የተሰራ መካነ መቃብር፣ የተለያዩ ጽናፅል፣ ቃጭል እና የመስቀል ስባሪዎች እንደተገኙ የሰሜን አቸፈር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ት ቤት ሀላፊ የሆኑት አማኑኤል ፀሀይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

የቁፋሮ ሂደቱ አለመጠናቀቁ የተጠቆመ ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ሂድት ከኖራ የተሰራ ከ3 ሜትር በላይ ቁመት ያለው ኹለት ቤተ መቅደስ፣ አምስት ሜትር በአምስት ሜትር ስፋት ያለው ቅኔ ማህሌት እና ቅድስት መገኘቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም አስር ሜትር በአስር ሜትር ስፋት ያለው በአንድ ቅድስት ኹለት ቤተ መቅደስ በሰሜን እና ደቡብ ጎን ለጎን የሆነ መሠረተ ህንፃ እንደተገኘ ተነግሯል፡፡ የእምነት አባቶች የቤተ ክርስቲያኑን ኹለንተናዊ ታሪክ የሚዳስስ መረጃ በማዘጋጀት ለወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ት ቤት መስጠታቸው ተገልጿል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች