የሶማሌ ክልል ፓርቲዎች አብሮ ለመሥራት ውይይት አደረጉ

0
526

በሶማሌ ክልል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት ጥቅምት 25/2012 ውይይት ማድረጋቸው ታወቀ።

ድርጅቶቹ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ውይይት በቀጣይ በጋራ የሚሠሩባቸውን ጉዳዮች በጹሑፍ የሚያዘጋጁ አምስት አባላት መሰየማቸውን የሶማሌ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ አስታውቋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ፓርቲዎች የዲል ወቤ ሕዝቦች ዴሞራሲያዊ ንቅናቄ፣ዱቤና ደግነ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የምዕራብ ሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲና የዴሞክራሲና ነፃነት ጥምረት መሆናቸው ዋልታ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ብሔራዊ ፓርቲዎች አብሮ ለመሥራት መስማማታቸው ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here