በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ሰደድ እሳት አጋጠመ

0
880

በትግራይ ክልል የሚገኘው የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ ደረሰበት። በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ መከሰቱን የቃፍታ ሑመራ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት አስታወቀ።

እሳቱ ጥቅምት 25/2012 ማምሻውን የተነሳ ሲሆን እስካሁን በ1 ሺሕ 500 ሄክታር የፓርኩ ክፍል ላይ ጉዳት ማድረሱን የፓርኩ ፅህፈት ቤት ገልጿል። የቃፍታ ሑመራ ኮሙኒኬሽ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትን ዋቢ አድርጎ ፋና ብሮድካስቲንግ እንደዘገበው  የእሳት አደጋው በፓርኩ በወራውራ፣ ጠበቆ፣ ኮርቸሊት እና ሰሊንጎቦ ቀጠናዎች የተከሰተ ሲሆን በሕገ ወጦች ምክንያት የተከሰተ ሊሆን እንደሚችልም የፓርኩ ፅሕፈት ቤት ተወካይ ሃብቶም ሃጎስ ተናግረዋል።

አደጋዉን ለመቀነስ የፓረኩ ጥበቃ ሰራተኞች ለመቆጣጠር ሙከራ አድርገዋል።በቀጣይ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የአከባበዉን ነዋሪዎች እና የሚመለከታቸዉ ሁሉ የድርሻቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በፓርኩ ውስጥ ዝሆንን ጨምሮ በርካታ በርቅየ እስሳትና አዕዋፋት እንደሚኖሩም የሚታወቅ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here