የኢትዮጵያን የጦር ኃይል በማጠናከር ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ውይይት ተካሔደ

0
695

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ዕዝ አዣዥ ከሆኑት ከጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ ጋር ዛሬ በቢሯቸው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ወታደራዊ ኃይልን ከማጠናከር አንጻር የነበረውን የረዥም ጊዜ የትብብር ግንኙነት በማስታወስ፣ የአገሪቱን ጦር ሠራዊት አቅም ለመገንባት የአጭር እና የረዥም ጊዜ ትብብርን በማጠናከር ላይ ተወያይተዋል።

በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘውን የተሐድሶ ሥራ ከማስቀጠል አኳያ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሠራዊቱን ብቃት ያለው ባለሙያ ማድረግ እና ለየትኛውም አካል እና የፖለቲካ ተቋም ምንም ዓይነት አድልዎ ሳያሳይ ወገናዊነቱን ለዲሞክራሲ ብቻ ያደረገ እንዲሆን ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አጽንዐት ሰጥተው ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here