በዘመቻ ሙሴ ተሳታፊ የነበሩት ጆርጅ ገትልማን በ80 ዓመታቸው አረፉ

0
445

በፈረንጆች 1980ዎቹ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ቤተ እስራኤላዊያንን ለመውሰድ በተደረገው እና ‹‹ዘመቻ ሙሴ›› የሚል ስያሜ በተሰጠው እንቅስቃሴ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸው እና በጀግንነታቸው በእስራኤላዊያን ዘንድ የሚዘከሩት ጆርጅ ገትልማን በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ጠንካራ የንግድ ሰው እየተባሉ የሚሞካሹት ጆርጅ በዘመቻ ሙሴ ወቅት አውሮፕላኖችን በማቅረብ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያ እስራኤላዊያንን ከኢትዮጵያ በሱዳን በማድረግ ወደ እስራኤል ማጓጓዝ እንደቻሉ ለማወቅ ተችሏል። ከዚሁ ባሻገር በአይሁዳዊነታቸው የማይደራደሩት የሚባሉት ጆርጅ በቢልጀም በተደረገው የአይሁዶች ጭፍጨፋም ላይ ከተረፉት አንዱ እንደሆኑ የታሪክ ድርሳናት ያወራሉ።

‹‹ጆርጅ ፂዮናዊ አይሁድ ነው። የእስራኤል ጉዳይ  እንደ ልጆቹ ኹሉ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ነው›› ሲሉ ለባለቤታቸው ያላቸውን ምስክርነት  ባለቤታቸው አለን ገትልማን ለእስራኤሉ የዜና አውታር የትኔት ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here