ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 27/2012

0
618

1-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት ባለፉት አስር ወራት 67ሽሕ 400 ትኬቶችን መሸጡን አስታውቆ፤ ሽያጩም በብር ሲሰላ 200 ሚሊዮን ብር እንደሚሆን አስታውቋል። (ኢትዮ ኤፍ ኤም)

……………………………………………………………..

2-የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከሕዳር 12-15/2012 ለሚካሄደው የፖሊዮ ቅድመ መከላከል ዘመቻ የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ መሆኑን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ናዲያ ሲራጅ ገልጸዋል።ክትባቱ ከ5 ዓመት በታች ላሉ 5 ሚሊዮን 373 ሺሕ 171 ሕፃናት እንደሚሠጥ የገለፁ ሲሆን ኤጀንሲውም 5 ሚሊዮን 977 ሺሕ 203 የክትባት መድኃኒቶችን እያሠራጨ እንደሚገኝ ተናግረዋል።የክትባት መድኃኒቶቹ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ኤጄንሲው አስታውቋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

……………………………………………………………..

3-የታጁራ-በልሆ መንገድ የጀቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑማር ጊሌ እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በተገኙበት ትላንት ጥቅምት 26/2012 ተመረቀ።የወደብ ከተማ የሆነችውን ታጁራን ከሰሜናዊ-ምስራቅ የኢትዮጵያ ክልሎች ጋር የሚያስተሳስረው 80 ኪሎ ሜትር የሚጠጋው ይሄው መንገድ በአካባቢው ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ላይ ቀላል የማይባል በጎ አስተዋዕጾ እንደሚኖረዉ ተገልጿል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………………………..

4-የይርጋዓለም አግሮ-ኢንዱስትሪ መንደር በ294 ሔክታር  መሬት በመገንባት ላይ የሚገኝ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲሆን  ዘርፈ ብዙ አገራዊ ጠቀሜታዎችን መሠረት አድርጎ የተነሳ ነው። በተለይም የወጪ ንግድ ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ጨምሮ  ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል።(ዶቼ ቬሌ)

……………………………………………………………..

5-በታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚገኘው አንድነት ፓርክ የልማት ድርጅት እንዲሆን የመተዳደሪያ ደንብ ለማፅደቅ በሒደት ላይ እንደሆነ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ ታምራት ኃይሌ ገለልጸዋል። ፓርኩ በቀን አምስት ሺሕ ጎብኚዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው አስታውቀዋል።ከመስከረም 20/2012 ጀምሮ ፓርኩን ለሕዝብ ክፍት በማድረግ ሥራ የጀመረው የአንድነት ፓርክ ባለቤት ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ከፓርኩ የሚገኘው ገቢም ለጽሕፈት ቤቱ ይውላል ብለዋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

……………………………………………………………..

6-በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች በ12 ወረዳዎች በ128 ቀበሌዎች ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሐብት ቢሮ አስታወቀ።በቢሮው የችግኝ ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ሂርጳ እንዳሉት የአንበጣ መንጋው ከጎረቤት ሶማሊያ የመጣ ሲሆን በሁለቱ ዞኖች ውስጥ በ23 ሺሕ 323 ሔክታር ሰብል ላይ ቢታይም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

……………………………………………………………..

7- ከፊ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቱሉ ካፒ የወርቅ ማውጫ ላይ ለመሰማራት የጀመረውን አሰራር አስመልክቶ ከኢትዮጵያ መንግስት አብሮ መስራት ሽርክና ማረጋገጫ ደብዳቤ እንደደረሰው አስታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

8- በ2012 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በንግድና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ አራት ድርጅቶች ከታክስ በፊት ብር 77.6 ሚሊዮን አተረፉ። (አዲስ ማለዳ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here