አምስተኛው የአፍሪካ የጨርቃ ጨርቅ የቆዳ እና የፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው

0
518

አምስተኛው አፍሪካ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳ እና የፋሽን ሳምንት እና አውደ ርዕይ ከጥቅምት 28 አስከ 30 በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚከናወን ተገለፀ።
በአውደ ርዕዩን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የጨርቃጨርቅ ልማት ኢንስቲትዩት ሚሲ ከተሰኘ መቀመጫውን ጀርመን እና ኬንያ ካደረገ አውደ ርዕይ አዘጋጅ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው።

በአውደ ርዕዩ ላይ ከ 280 በላይ ዓለም ዐቀፍ አምራቾች እና ላኪዎች እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን፣ ከ 25 አገራት ከ5000 በላይ የንግድ አጋሮች ፈጠራቸውን እና ምርቶቻቸውን ለማሳየት እንደሚሰባሰቡ ይጠበቃል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በጎብኚዎች ቁጥር ከ 20 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል። ጀርመን ፖርቹጋል እና ፈረንሳይ ባለሞያዎቻቸውን መላካቸው የተገለፀ ሲሆን ከምሥራቅ አፍሪካ ከቻይና ፓኪስታን የተውጣጡ ባለሙያዎች እንደሚገኙም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በእንስሳት ሃብት ያላትን ሰፊ አቅም በመጠቅም ከዘርፉ በርካታ ጥቅሞችን እንድታገኝ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ከዚህ ቀድም ሲላክ የነበረውን ጥሬ ቆዳ እና የለፋ ቆዳ ላይ እሴት በመጨመር ወደ ውጪ ሀገራት ለመላክ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።

ከጨርቃ ጨርቅ ምርቶች በባለፈው በጀት ዓመት ከ 155 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በ 2012 ሩብ ዓመት የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ምርቶችን ወደተለያዩ አገራት በመላክ 52 ሚሊዮን ብር ከዘርፉ ለመሰብሰብ ተችሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 53 ጥቅምት 29 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here